| 01.12.2008 | 17:00 UTC
ናይሮቢ፣ የ ተ መ ድ፣ ለሶማልያ የ 20009 እርዳታ ከፍ እንዲል ተማጸነ፣
የተባበሩት መንግሥታት፣ ከሞላ ጎደል ገሚሱ የሶማልያ ህዝብ በመጪው 2009 ጎርጎሪዮሳዊ ዓመት 918 ሚልዮን ዶላር ያስፈልግዋል በማለት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተማጽኖውን አሰማ። ዓምና ከተማጽኖው፣ 70 ከመቶው ተሟልቶ 662 ሚልዮን ዶላር እርዳታ ቀርቦ ነበር። የተባበሩት መንግሥታት የሰብአዊነትና የመኖሪያ ጉዳይ አስተባባሪ ማርክ ቦውደን፣ 918 ሚልዮን ዶላር የሚያስፈልግው ፣ የህዝቡ ቁጥር በመጨመሩ ብቻ ሳይሆን የማቅረቢያው ዋጋም በመናሩ መሆኑን ገልጸዋል። 300 ሺ ያህል ህጻናት በምግብ እጦት የተጎዱ ሲሆን እጅግ ያገረሸው የእርዳታ ሠራተኞች ጠለፋና የባህር ላይ ውንብድና ብዙዎች የእርዳታ ፕሮጀክቶች እንዲዘጉ አስገድዷል።




