| 01.12.2008 | 17:00 UTC
መቅዲሹ፣ በአደን ባህረ-ሰላጤ ስደተኞቹ ሰጠሙ፣
በየመን የባህር ጠረፍ ጠባቂዎች ላለመያዝ ፣ ህገ-ወጥ በሆነ መንገድ ሰዎችን በአደን ባህረ-ሰላጤ በኩል ወደ የመን የሚያሸጋግሩ ሰዎች 240 ስደተኞች ከመርከብ ወደ ባህር አየዘለሉ እንዲዋኙ በማስገደዳቸው 18 ሲሰጥሙ ከ 70 በላይ የሚሆኑት ደብዛቸው መጥፋቱ ተነገረ። የተረፉት ደቡብ የመን ከተማ ፣ አህዋር መግባታቸው ተገልጿል ። ስደተኞቹ፣ በአመዛኙ ከሶማልያ ጥቂቶቹም ኢትዮጵያውያን እንደነበሩ ተመልክቷል።




